January 2, 2021 By Oromia Post

Photo: dmz.de
ባላለፉት 40 አመታት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩ እና በሚልዮኖች የሚቆጠር ሰዎች፣ ከገጠሩ ወደ ከተሞች እንደፈለሱ ጸሃይ የሞቀው እውነታ ነው። በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ እያደገ ካለው የህዝብ ቁጥር ጋር፣ አብሮት ሊሄድ የሚገባው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የምግብ አቅርቦት፣ ስራ ፈጠራ እና የመኖሪያ አቅርቦቶች ሊመጣጠኑ አልቻሉም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስራ ፈላጊዎች፣ ከተሞችን አጥለቅልቀዋል። የሃገሪቱም ዋና ከተማ ፊንፊኔም፣ እልፍ፣ ባለ ዲግሪ፣ ስራ ፈላጊዎች መሸሸጊያ ሆናለች። የመዲናይቱ ህዝብም ወደ 10፣000፣000 እንደሚጠጋ አንዳንድ የህዝብ ጥናት አውዶች ይተነብያሉ። ከዚህ ሁሉ ህዝብ ወደ ከተማ መፍለስ ጋር ተደምረው፣ ሊመጡ የሚችሉ ችግሮችን መገመት አይከብድም። የዚህችም አጭር ጽሁፍ አላማ፣ ይህ የህዝብ ፍልሰት በአካባቢዋ ያሉ አርሶ አደሮች እና የፊንፊኔ ዙሪያው ኦሮሞዎችን ህልውና ለመታደግ አቅጣጫ ለማሲያዝ ነው።
ዛሬ እድሜው በ30ዎቹ አካባቢ ያለ አንድ ሰው፣ ስለ ፊንፊኔ ከተማ መስፋትና ከአዳማ ከተማ ያልተናነሰ መሬት፣ በተቀናጀ ሁኔታ፣ በሌቦች እና ሆድ አደር ኦሮሞዎች መሪነት፣ መዘረፉን የሚጠፋው አይመስለኝም። ይህንን ሃቅና እውነታ፣ የኦሮሞን ህዝብ በማዋረድና ማሸማቀቅ ሚተዳደሩ ግለሰቦች፣ አልፎ አልፎ እራሳቸው፣ ሲመሰክሩ ሰምተናል፣ አይተናል፣ አንብበናል። እንዲሁም፣ ከ30 እና 40 አመት በፊት አባቱ ወይንም እናቱ 600 ኪ.ሜ. እና ከዛ ባላይ አቋርጠው የመጡ ከተሜዎች፣ ዛሬ፣ እራሳቸውን አዲስ አበቤ እያሉ፣ የገላን፣ የቃሊቲን፣ የቦሌን፣ የቡልቡላን፣ የሱሉልታን፣ የለገ ጣፎን፣ ወዘተ አርሶ አደር ልጆች መጤ፣ ወራሪ ወዘተ ሲሉ ሰምተናል፣ አይተናል፣ አንብበናል። ይህ ውለታ ቢስ፣ ወጭት ሰባሪ፣ ሃይል፣ ከ 4፣000፣000 ሚልየን ያማያንሱ የቱለማ ኦሮሞዎችን ከሸገርና እና ዙሪያዋ አፈናቅሎ፣ ወደ አርሲ፣ ባሌ፣ ሃረርጌ፣ ጅማ፣ ቦርና እና ኢሉ አባቦር ማባረሩ ሳይንስ ዛሬም፣ በእንቡጥ ህልመኛ የኦሮሞ ካድሬዎች ታግዘው፣ የተቀሩትን አርሶ አደሮች ሊያጠፉ እየሰሩ ነው።
ህዝባችንን ከዘረፋ እና ብዝበዛ ለመታደግ፣ ከታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ጥሩ አቅጣጫን ያሲዛሉ ብለን እናስባለን፡
የፊንፊኔ ከተማን ድንበር በኬላዎች መዝጋት እና በከተማዋ አዋሳኝ ቀበሌዎች ዙሪያ ከ 50 የማያንሱ፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጣቢያዎችን (Police Stations) ማቋቋም። ከነዚህ ኬላዎች መልስ ምንም አይነት የኮንዶሚየም ፕሮጀክቶች እንዳይጀመር እገዳ መጣል። የኮንደሚንየም ግንባታ እና መሬት ዘረፋን፣ ሆን ብለው፣ የወያኔ ጁንታው ጭራ ጭራ ስር እየተከተሉ መሬት ሲወሩ የነበሩና ለወደፊትም ያቀዱትን ከግስጋሴያቸው ያስቆማል። “ኦሮሞ እንዴት የከተማዋ አስተዳዳሪ ይሆናል?” እያለ፣ የቱለማ መሬት ላይ አይኖቹ የተደገኑ የመሬት ፍቅረኛን መዋጋት የእያንዳንዱ ኦሮሞ የውዴታ ግዴታ ነው። ይሄን ኦሮሞ-ጠል እና ፍቅር መሬት ጋር ብቻ የያዘውን ሃይል ለማስቆም፣ ሳይፈሩ እና ሳይቅለሰለሱ የሚሰሩ ጠንካራ የኦሮሞ ወጣቶችን በብዛት በዙሪያው መሾም። ለፈስፋሳ እና የዘበኝነት አባዜ የያዘውን ኦሮሞ ማስወገድ። ለራሱም፣ ለህበረተሰቡም መጥፋት ምክንያት ነውና።
ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚመጣውን ውሃ፣ ንብረትነቱ፣ የኦሮሚያ ክልል የሆነ ፊንፊኔ ውሃ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ማቋቋም እና ንብረትነቱን ማስተላለፍ። የዚህን ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ በፊንፊኔ ዙሪያ ከተማ ውስጥ መገንባት። ይህ ኮርፖሬሽን፣ የውሃ ዝርጋታን፣ የውሃ ክፍያ ገቢን መሰብሰብ፣ የውሃ ጥበቃን እና ልማትን እንዲመራ ማድረግ። ከኦሮሞ አርሶ አደር ጉያ ውሃ መጠጣቱ ሳያንስ ከተማው፣ ከውሃ ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለራሱ የሚያደርግበት ዘረፋ፣ በየትኛውም አለም ፍትሃዊነት የለውም። ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። የጣናን ውሃ፣ መቀሌ በነጻ ወስዳ እንድትሸጠው ስለማይፈቀድ ማለት ነው።
ከዚህ የውሃ ብቻ የሚገኘውን በትንሹ ከ 5 ቢለየን ብር በላይ ገቢ፣ ለኦሮሞ አርሶ አደሮች የመሰረተ ልማት ግንባታ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞችን ለማሳደግ ይውላል። ይህንን፣ የህዝብ ሃብት ከአንዱ ክልል ወስዶ ለሌላው መስጠት ሳያንስ፣ ሌላው ሽጦ ሚለማበትን ቀመርት ማስተካከል ፍትሃዊነት ነው። የኦሮሚያ ክልል ጨፌ ይህንን፣ ያለምንም ማመንታት በአስቸኳይ ሊተገብር ግድ ይላል። ሞዴል፡ https://www.wsscwater.com/home.html
ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞችን ማዕከል ያደረገ የኢንደስትሪ ፓርኮችንን መዘርጋትና በእነዚህ እንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ፣ የኦሮሞን ባለሃብቶች እና የአከባቢውን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ፕላን ማድረግ። ለዚህም የሚያግዙ፣ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮሚሽን ማቋቋም እና መተግበር።
በኦሮሚያ ክልል ከተሞች ሁሉ፣ የኦሮሞ ዳይስፖራ ከተሞችን ፕላን ማድረግ። ኦሮሞ ዳይስፖራ ከተሞችን በመቀየስ፣ ከ2፣000፣000 የማያንሱትን የኦሮሞ ዳይስፖራ፣ ፊንፊኔ ብቻ ሳይሆን፣ በተወለዱበት አካባቢ፣ ዘመናዊ መሰረት ያላቸው ከተሞችን ማስፋፋት። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በ አስርት ቢለየኖች የሚገመት ገንዘብ፣ ወደ ኦሮሚያ ክልል በህንጻ ግንባታ፣ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ ወዘተ ማምጣት ይቻላል። የዳይስፖራ ከተሞች፣ ከፊንፊኔ ዙሪያ መሬት ዘረፋ ወደ፣ ክፍለ ሃገር ከተማ ዘረፋ እንዳይስፋፋ፣ እራሱን የቻለ፣ የዳይስፖራ ኢንቨስትመንት እና ከተሞችን ተቆጣጣሪ ገለልተኛ ተቋም ማቋቋም። ይህ ፕላን፣ ከፊንፊኔ ተገዳዳሪ የሆኑ፣ ንጹህ፣ በቴክኖሎጂ የረቀቁ፣ መሰረተ ልማታቸው የዳበረ እና ለኑሮ ተመራጭ የሆኑ sustainable ከተሞችን ለመገንባት ያስችላል።
የፊንፊኔ ከተማ ወጣቶች፣ ስራ አጦች፣ ወዘተ እየተባለ፣ በከተማይቱ ዙሪያ ሚስፋፉ እና የኦሮሞ ወጣቶችን የማይጠቅሙ የመሬት ወረራዎችን ማስቆም። በፊንፊኔ ውስጥ የሚኖሩ እና የሚሰሩ ኦሮሞዎችን፣ በከተማይቱ ውስጥ፣ መብታቸው እና ጥቅማቸው እንዲጠበቅ፣ በሳል እና ቆራጥ ወጣት አመራሮችን በብዛት መቅጠር እና ማደራጀት።
ፊንፊኔ ውስጥ ያሉ የፌድራል መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት ኮርፖሬሽኖች እና ድርጅቶች ውስጥ፣ ለኦርሞ ስራ ፈላጊዎች በኮታ የስራ እድል እንዲሰጥ ማድረግ ወይንም መጠየቅ። አዎን፣ የኦርሞ ህዝብ፣ ህጉ በሚፈቅደው፣ በሙያ ብቃቱ እና በዲሞክራሲያዊነት ብቻ ላይ የታገዘ የስራ ቅጥር እና ምደባ ከተደረገ ያለምንም እርዳታ፣ ብዙ መቶ ሺ የፌድራል ስራዎችን በጁ ያስገባል። አዎን፣ ፈሪ እና ሸምቃቃ ኦሮሞዎች፣ የአህዳዊው ዘመን ትርፍራፊዎች በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ሲልመጠመጥ ይታያል። የስራ ቅጥርን፣ እና የብሄር ስብጥር ዳታን መልቀቅ ኦሮሞውን በጣም ይጠቅማል። ለምን? በተግባር ተጠቃሚው ማን እንደሆነ ስለሚታወቅ። Data! Data!
የህዝብ ቆጠራን በአፋጣኝ መጠየቅ፣ እና በፓርላማው ሚጸድቁ በጀቶች፣ በህዝብ ብዛት እንዲገለጹ መጠየቅ። የኦሮሞ ህዝብ population-based reimbursement መጠየቅ አለበት። ይሄ ደግሞ ስጦታ ሳይሆን፣ የፍትህ እና እውነት ጉዳይ ነው። ክልሉን ዘርፎ ወደ መዲናይቱ ሃብት ማሸሽ ወይንም ክልሉን ዘርፎ ሌላውን ማልማት ፍትህ ስላልሆነ። እያንዳንዱ የኦሮሚያ ተመራጭ ይሄንን መጠየቅ አለበት።
በኦሮሚያ ክልል ሚዘዋወሩ ተሽከርካሪዎች፣ ግብር ቀጥታ ለክልሉ ክልል እንዲከፍሉ ማድረግ እና የመንገድ ላይ ኬላዎች ገቢ ወደ Oromia State Highway Administration (OSHA) አዲስ ኮርፖሬሽን ስር እንዲገባ ማድረግ። አዳማ ላይ ብር ሰብስበህ፣ ሌላው የሚጫማበት ዘረፋ ወደ ቀብር ሊሸኝ ግድ ይላል። ቢሾፍቱ ላይ ቁጭ ብሎ ዘረፋ ይቁም! All Toll-Roads belong to the State. ይሄ የምዕራቡ ሃገሮች ሚሰሩበት ነው። የፌድራል Highway የሚባል ነግር የለም። ሞዴል፡ Home (maryland.gov)
በፌድራል ገቢዎች የሚዘረፉ የኦሮሚያ ከተሞች፣ ዘረፋው እንዲቆም እና የክልሉ የኢኮኖሚ ሉአላዊነት እንዲጠበቅ ማድረግ። ከጎንደር ከተማ ሚለቀም ግብር ለጅማ ከተማ ሆኖ አያውቅምና። በዚሁ ሎጂክ፣ ከአወዳይ፣ ግብር ሰብስበህ፣ ሸገርን ምታሳብጥበት ምክኛት የለም። የቄሳርን ለቄሳር!
የዋና ከተማይቱ ህልውና በኦሮሚያ ክልል ላይ እንደሆነ ሁሉ፣ ከተማዋ የምትሰበስበው ግብር፣ በቀጥታም ሆነ፣ በተዘዋዋሪ ከኦሮሞ ህዝብ ነው። የከተማዋ መሬት፣ ውሃ፣ የግብርና ምርቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ ሸቀጦች እና የግንባታ ግብአቶች የሚመነጩት በአብዛኛው ከዚሁ ክልል ነው። ቲማቲም እና ሽንኩርት ከትግራይ ሲገባ አላየነም። ድንጋይ፣ አፈር እና የግንባታ እንጨት ከባህር ዳር ሲመጣ አላየነም። የአትክልት ተራ ነጋዴ፣ ህይወቱ በ ቆቃ አካባቢ፣ በአዋሽ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ እና አርሲ አርሶ አደር ምርት ላይ ጥገኛ ነው። የወተት እና ተረፈ ምርቱም ምንጭ የሰሜን ሸዋ ኦሮሞ ነው። ስንዴ እና ገብስ ነጋዴውም፣ ከሱማሌ ክልል እህል ሲያገባ አላየንም። ስለዚህ፣ የከተማይቱ ግብር ከ65% በላይ ምንጩ የኦሮሞ ህዝብ እንደሆነ፣ ሰው ሳይቀር፣ ሳር ቅጠሉ ይመሰክራል። ይሄንን ጨፌ ኦሮሚያ፣ በሚቀጥለው በጀት አመት፣ ለፌድራል መንግስት ማቅረብ አለበት።
በተቀናጀ መልኩ፣ ከመንግስት ደጋፊ-መሳይ እና ተቃዋሚ የአማርኛ ሚድያዎች የሚደረጉ የኦሮሞን ህዝብ እንደ ወራሪ፣ አራጅ፣ ዘራፊ አድርጎ የመሳል ዘመቻ እንዲቆም ጨፌው መጠየቅ አለበት። ይሄ ከባድ ወንጀል ነው። በጣም አደገኛ። እንደ demonization እና ህዝብን በጅምላ ማዋረድ ለጦርነት ሚገፋ የለም። አስቁሙልን በአስቸኳይ! በ30 አመት ሰምተን የማናውቃቸው፣ ስድቦች፣ እና ህዝቡን የማሰይጠን ስራ ከቤተመንግስቱ፣ በቅርብ ርቀት ያሉ ሚድያዎች ሲዘሩት መታገስ አቅቶናል። የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስተር ባለበት ሃገር፣ በየእለቱ ሳያቋርጡ፣ ኦሮሞ ላይ የፕሮፐጋንዳ ዘመቻ፣ እንዲከፈት የተፈለገ ይመስላል። የሚድያዎችን ስም እና ግለሰቦችን ስም መጥቀስ፣ በነሱ ደረጃ መውረድ ስለሆነ፣ ይሄንን አውቃቹ፣ የኦሮሚያ የብልጽግና አመራሮች፣ አንድ ልትሉ ግድ ይላል። ጋላ፣ ወራሪ፣ አራጅ፣ ወዘተ እያሉ ከሚሰድቡን፣ እና፣ ከመሬታችን ጋር ፍቅር የያዛቸውን ሰዎች፣ በአንዲት ደብዳቤ ማዘጋት ይቻል ነበር። አስቁሙልን በአስቸኳይ።